24/11/2025
ታሪካችን ተመሳሳይ ነው
ለመጀመርያ ግዜ ትልቅ ስራ ያገኘሁበት የሰራሁበት ተስፋ ያየውበት ቤት ነው ።
ቆይ ሙሉ ታሪኩን ልንገራቹ
2009 ላይ አንድ ባለ ሃብት የብረት ስራ እንደምሰራ የሚያውቅ ይህ የምታዩትን ቤት ሙሉ ስራ እንድሰራለት ዋጋ አውጥቼ እንድነግረው ይዞይኝ ይሄዳል
(ትልቅ ሰው ናቸው አንቱ እያልኩ ልቀጥል)
ቤቱ G+3 ነው ከዛ ደሞ ቴራስ አለው
ሙሉ በረንዳውን እና የውጭ በር ነው እንድሰራላቸው የሚፈልጉት።
ሳይዛቸውን ወሰድኩኝ : ስለስራው ጥራት እናአውጥቼ እንድነግራቸው አውርተን ተለያየን
በስማም ያሳለፍኩት ቀን አቤት ስራውን ቢሰጡኝ አቤት ይሄን ስራ ብሰራው በቃ ሙሉ ቀን ብቻዬን ሳወራ ዋልኩኝ ፣ ሂሳቡን ወድያው ያወጣው ቢሆንም : ተንገበገብ ቸኮልክ እንዳይሉኝ አሳደርኳት በበነጋው 78,000 ብር ብዬ ነገርኳቸው : በጣም በዛ ኤልያስ አሉኝ
ትንሽ ካወራን በኋላ። በ 75,000 ብር ተስማማን ልብ አድርጉ G+3 ቤት ከነ በሩ በ75000 ብር አሁን እኮ ለውጭ በሩ ራሱ አይበቃም ምን ያህል ኖሮ እንደቆሰው ማሳያ ነው )
በቃ ከ15 ቀን በኋላ ቀብድ ሰጥሃለው ትጀምረዋለህ ተባልኩ።
15 ቀን ራቀ በጣም : እናንተ ሩቅ አታውቁም : : ራቀ ስላቹ እንዲ መስሏቹ በጣም በጣም ነው የራቀው 15 ቱን ቀን ሌላ ሃሳብ የለኝም ሃሳባቸውን እንዳይቀይሩ ምናለፋቹ ያላሰብኳቸው ነገሮች የሉም ቀኑ ደረሰና ስጠብቅ ስጠብቅ ብውል ወፍ 16,17,18 እያለ ቀኑ መጨመር : ከዛ ደወልኩኝ ምን ማለት እንዳለብኝ ራሱ አላውቅም: ብቻ ደወልኩኝ
እንዳነሱት ሰላም ኤልያስ ጠፋው አደል ቆይ አንዳንድ ነገሮች አልሞላ ብለው ነው ደውልልሃለው
🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺
ቀኖች በጣም መሄ ጀመሩ መደወልም ሼም ነው ከዛ እርግፍ አድርጌ ተውኩት :አመት አለፈው
🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺🥺 ልክ በአመቱ ሙሉ ለሙሉ ከጭንቅላቴ ከወጣ በኋላ ደውለው :
ኤልያስ እስኪ ያንን ነገር ፈጠን አድርገን እንጨርሰው አሉኝ 😱😱😱😱 ማመን ነው ያቃተኝ በቃ ሌላ ሰው አሰርተዋል ብዬ ነበር ያሰብኩት :
እሺ ግን የተውት መስሎኝ ልኬቱ ጠፍቶኛል ቀብድ አስገቡልኝ እና ሄጄ ልለካው ተባባልን
አዋሽ ባንክ አለህ ? አዎ
( የለኝም እኮ ደሞ በዚ ቢጠፉስ ብዬ ነው) ቤት ስለሆነ ማታ ልክሎታለው አልኳቸው እና ስሮጥ ሄጄ አወጣው።
እዚህ ጋር ልብ አድርጉ ከአንድ አመት በኋላ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይኖረው ነው የሰራሁላቸው ምክንያቱም እቃ ያን ያህል አይጨምርም ነበር ። አሁን እኮ
እንደውም ባለፈው የዛሬ ሳምንት ቅዳሜ ቀን MDF ልጭን ብዬ
ጠዋት 2:30 ላይ ዋጋ ቼክ አድርጌ 3350 ብር ብለውኝ መኪናው ወደ 5:00 አካባቢ ሲሄድ 3700 ዞሮዞሮ አጠያይቆ መገዛት የግድ ስለሆነ በ3600 ብር 35 mdf ገዛው ይሄ ማለት ወደ 8700 ብር ኪሳራ በ2 ሰዓል ልዩነት ውስጥ😴😴😴😴😴
ብቻ አካውንት ላኩላቸው 20,000 ብር አስገቡልኝ: አኡፍፍፍፍፍፍፈፈ። ስሜቱን አታቁትም በቃ ብቻዬን ስፈግግ ዋልኩኛ 🥰🥰🥰😀😀😀😀🥰🥰🥰🥰😀😀😀😀😀🥰🥰🥰🥰😀😀😀😀🥰🥰🥰🥰😀😀😀🥰🥰🥰😀😀😀🥰🥰🥰😀😀😀🥰🥰🥰😀😀😀🥰🥰🥰😀😀🥰🥰🥰😀🥰😀🥰😀🥰😀😀🥰😀🥰😀🥰😀😀🥰😀🥰😀 ምን አለፋቹ እንዲህ ነው የዋልኩት
።
ከዛ በአንድ ወር ውስጥ ስራውን ሰርቼ ጨረስኩ
ያኔ ነው
. #ከፀዴሰኞጋራ እምተለዋን መለያ እና መፈክሬን ማለት የጀመርኩት
( የሆነ ቀን የሰራነውን ፎቶ ካገኘውት edit አድርጌ ጨምረዋለው)
አንዳንድ ቀለል ያሉ ማሽኖችን ገዛው ከዛ በትልቁ ማሰብ እንዳለብኝ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ ።
አሁን
#ተመስገን 🙏🙏🙏🙏
የ 750,000 ብርም ስራ ብዙ ግዜ ሰርተናል ስሜቱ ግን እንደ 75,000 ብሯ አይሆንም