14/05/2026
የጥንቃቄ = መልዕክት
ዛሬ ግንቦት 06/09/2018ዓ/ም በዕለተ ሀሙስ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በግምት በምሆንበት ጊዜ ስሙ ሁሴን ወዕሌቦ ሁሎሮ አድራሻው ከንባታ ዞን አድሎ ዙርያ ወረደ ሸሸራ ቸፌ ቀበሌ ነዋሪ የሆነውን ግለሰብ አንድ አርሶ አደር ግለሰብ ስሙ አቶ አበራ የምባል አድራሻው ሀ/ቁ/ከ/በሜጦ ቀበሌ በጋለቶ ቀጠና ነዋሪ ሲሆን ግለሰቡ በሜጦማ ቀበሌ በዋንጃ ዋልድያ በቡሼ ንዑስ መንደር ውስጥ የዘረውን ቦቆሎ ለማስኮተኮት
ከዝህ በላይ በስም የተጠቀሰውን ሟች ሁሴን ወዕሌቦ ሁሎሮ የተባለውን ግለሰብ ቦቆሎውን እንድኮተክትለት በገንዘብ 700ብር ተስማምቶ
ለስራ ያስገባዋል። ይህ ግለሰብ ስራውን የጀመረው ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አከባቢ ስሆን ለዝህ ግለሰብ/ሟች/የአቶ አበራ ባለቤት ወደ በቆሎ ማሳ ምሳና ውሃ ይዛለት ትሄዳሌች
ምሳውን ሴትዮዋ ስትወስድለት ሟቹ በኩትኳቶ ስራው ላይ እንደነበር ትናገራሌች ከዝያ ሴትዮዋ ሰራተኛውን ወደ ጥላ ሆነህ ምሳህን ብላ ትለዋሌች ከዝያ ሟቹም እሽ ይልና እዝህ ጋ አምጭልኝ ብሎ በቆርቆሮ ወደታጠረው አጥር ጥግ ሄዶ ቁጭ እንዳላ ምሳውንም ሳይበላ የመጨረሻ ምሳውን የወሰደችለት ሴትዮዋ ምግቡንም ከዛንብሏም ሳታወጣ እዛቹ ተደግፎ የተቀመጠውን የቆርቆሮ አጥሩን እንደተደገፋም በዛችው ቅጽበት ምግቡንም ሳይበላ ህይወቱ ልያልፍ እንደቻላ ትናገራሌች
በወቅቱም የሟችን ሁኔታ የተመለከተችው ሴትዮ ሌሎች ሰዎችን ጠርታ ስለሟቹ አሟሟት ሁኔታ ታስረዳሌች ከዝያ በመቀጠል ለፖሊስ ይደዎላል በፍጥነት የደረሰው ፓሊስም የሟቹን ማንነትና አድራሻ ለማወቅ በአስክሬኑ ላይ መታወቂያ ይፈልግና ልያገኝ አልቻለም ከዝያም ሟቹን ከሰራተኛ ተራ አምጥቶ የቀጠረውን ግለሰብ/አቶ አበራ የተባለውን አስጠርቶ
ይህን ግለሰብ/ሟች/ስሙንና አድራሻውን ጠይቄህ ነበር ወይ? ስል ፓሊስ ይጠይቀዋል ስጠይቀው ስሙን አልጠየኩም አድራሻውን ስጠይቀው አድሎ ዙሪያ ወረዳ ከሸሸራቸፌ እንደመጣ ነግሮኛል መታወቂያ ግን አልጠየኩትም ስል ለፖሊስ ይናገራል።
ከዝያ ሪፖርት የተደረገለት የቁሊቶ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ረ/ኢ/ር ሹክራላ ሸ/ሱጋቶ የወንጀል መከላል ፓ/አባላትንና ፓትሮል መኪና ይልካል አስክሬኑ በዝህ መኪና ተጭኖ ምናልባት የምያውቀው ሰው ከተገኘ በምል ወደ ሰራተኛ ተራ ተወስዶ የምያውቀው ሰው ከተገኘ ተብሎ ስጠያያቅ የሟችን ሙሉ ስሙንና አድራሻውን የምያውቅ ሰው ተገኝቷል በዝህ መልኩ ለማወቅ ተችሏል።
ዘመድ የምሆንለትን ሰው በዝህ መልኩ እንድመጣ የተደረጋ ስለሆነ
አሁን ለህብረተሰባችን የምናስተላልፈው ዋናው
መልዕክታችን ማንኛውንም የቀን ሰራተኛ ለስራ ስንፈልግ / ስንቀጥር አስቀድመን ስሙንና ሙሉ አድራሻውን በትክክል የምገልጽ ብቻል የድጅታል መታወቂያ ካልሆነም ብያንስ የቀበሌ መታወቂያ መያዙን ያረጋግጡ።