Sagal Jama

ራስን አለማመን !ለምን ራሳችንን እንደማናምን ታውቃላችሁ?ዋነኛው ምክንያት ብዙ ጊዜ ለራሳችን ቃላችንን አጥፈናል። ሰራለሁ ብለን አልሰራንም። ጀምራለሁ ብለን አልጀመርንምም ብቻ ብዙ ብዙ ጊዜ ...
01/12/2023

ራስን አለማመን !
ለምን ራሳችንን እንደማናምን ታውቃላችሁ?
ዋነኛው ምክንያት ብዙ ጊዜ ለራሳችን ቃላችንን አጥፈናል። ሰራለሁ ብለን አልሰራንም። ጀምራለሁ ብለን አልጀመርንምም ብቻ ብዙ ብዙ ጊዜ ለራሳችን ቃል ገብተን ቃላችንን አጥፈናል።

ራስን መጠራጠሮ እጅግ በጣም መጥፎ ባህሪ ነው። ትልቁ ህልም ገዳይ ነገር ራስን መጠራጠር ነው።"

ራስህን ለመቀየር ህልም አነግበህ ስትነሳ ትልቁ እንቅፋት የሚያጋጥምህ መውደቅ መነሳት ሳይሆን እኔ ግን እችለዋለው ፣ እውነት ይሄ ይሆናል ፣ ይሳካል ? የሚል የማያቋርጥ ድምፅ መኖር ነው።

ራስን ከመጠራጠር ወደማመን ባህሪ መምጣት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ሊቅነትን ይማሩ።

🗝 በማንኛውም ሁኔታ በየትኛውም ወሬ እና ሐሳብ  በመጨናነቅ እንዳትመላለሰ አቋም ✊መያዝ አለብህ🔑
26/11/2023

🗝 በማንኛውም ሁኔታ በየትኛውም ወሬ እና ሐሳብ በመጨናነቅ እንዳትመላለሰ አቋም ✊መያዝ አለብህ🔑

ጭንቅላትን (አዕምሮን) ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከ...
21/11/2023

ጭንቅላትን (አዕምሮን) ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከል ነው፡፡ የቆሸሸ ደግሞ ይጣላል እንጂ አይጠቅምም፡፡

መስመሩን የጠበቀ አመጣጥ መሆኑን አረጋግጥ‼️በፍቅር ጎዳና ውስጥ አንድ ሰው ወደ አንተ የመጣበት አመጣጡ ከአንተ ጋር የመቆየቱንና ያለመቆየቱን ሁኔታ ይወስናል፡፡ ከዚህ በታች ያሉት መስፈርቶች...
07/11/2023

መስመሩን የጠበቀ አመጣጥ መሆኑን አረጋግጥ‼️

በፍቅር ጎዳና ውስጥ አንድ ሰው ወደ አንተ የመጣበት አመጣጡ ከአንተ ጋር የመቆየቱንና ያለመቆየቱን ሁኔታ ይወስናል፡፡ ከዚህ በታች ያሉት መስፈርቶች አንተ ባሉህ ጤናማ መስፈርቶች ላይ ተጨማሪ መዋጮ ያደርጉልሃል፡፡

ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት፡፡
03/11/2023

ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት፡፡

Black box Thinking)ጥቁር ሳጥን (Back Box) ማለት በአውሮፕላኖች ላይ የሚገጠም የበረራ መረጃዎችን የሚሰበስብ መሳሪያ ሲሆን  ይህ ሳጥን የአብራሪውን ንግግሮች ጨምሮ ሌሎች በር...
31/10/2023

Black box Thinking)

ጥቁር ሳጥን (Back Box) ማለት በአውሮፕላኖች ላይ የሚገጠም የበረራ መረጃዎችን የሚሰበስብ መሳሪያ ሲሆን ይህ ሳጥን የአብራሪውን ንግግሮች ጨምሮ ሌሎች በርካታ የበረራ መረጃዎችን በፍጥነት ማከማቸት የሚችል ሪኮርደር ነው፡፡ ስለሆነም የአንድን አውሮፕላን አደጋ መንስዔ ለማወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የአየር መንገዶችን ያህል ስህተቶችን የሚጠቀም ኢንዱስትሪ የለም። ሳለን በርባር የተባለው ካፒቴን በሚገርም ሁኔታ በሆድሰን ወንዝ ላይ አውሮፕላኑን ማሳረፍ ከቻለ በኋላ የሚከተለውን ፅፏል፡፡ “በአቬሽን ውስጥ የምናውቃቸውን እያንዳንዳቸውን ነገሮች፣ በበረራ መመሪያው ውስጥ ያሉትን እያንዳንዳቸውን ህጎች እና የምንጠቀምባቸውን እያንዳንዳቸውን ሥነ ሥርዓቶች በሙሉ ለማወቅ የቻልነው የሆነ ቦታ ላይ፣ የሆነ ሰው ሞቶ ነው፡፡” አደጋ በደረሰ ቁጥር ከዚያ በኋላ ያሉት በረራዎች ደህንነት የበለጠ አስተማማኝ እየሆነ ይሄዳል፡፡ ይህ መርህ (የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ እንበለው) በሌሎች የሕይወት ዘርፎች ላይም መተግበር የሚችል ጥሩ የአዕምሮ መሳሪያ ነው፡፡

የሰው ልጆች የአቬሽን ኢንዱስትሪው ፍፁም ተቃራኒ ናቸው።ምክንያቱም እውነታን ተቀብለው ሪከርዳቸውን የመተንተን ልማድ ያላቸው በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።ይህ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ነገሮችን ይጠይቃል፡፡ 1) የመቀበል አቅም እና 2) የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ። መጀመሪያ እውነታን መቀበል አለብህ፤ ስትቀበልም ሙሉ በሙሉ ይሁን። በተለይ ያልወደድካቸውን የእውነታውን ክፍሎች። በወቅቱ ከባድ ሊሆንብህ ይችላል። ነገር ግን የግድ ማድረግ አለብህ። ዋጋውንም በኋላ ታየዋለህ። ሕይወት ቀላል አይደለችም። ጥሩ ሕይወትን እየኖርክ እንኳን የውድቀትን ፅዋ መጋትህ አይቀርም። መሳሳት ችግር የለውም። ዋናው ቁልፍ ስህተቱ ለምን እንደተፈጠረ ለይቶ ማስተካከያ ማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም ችግሮች እያደር ይጣፍጡ ዘንድ የወይን መጠጦች አይደሉም።

የምናየውን ነገር የምንወደው በሆነ ጊዜ እውነታን መቀበል ቀላል ነው፡፡ ችግሩ የምናየውን ነገር የማንወደው በሆነ ጊዜ ነው፡፡ ሩሴል ምሳሌ ያነሳል። "የፃፈው ተውኔት አንድም ቀን ተዋጥቶለት የማያውቅ ደራሲ “ተዋናዮቹ ብቃት የላቸውም የሚለውን የሚያፅናና
መደምደማያ ሲይዝ ማየት የተለመደ ነው።” አንተ ተውኔት ላትፅፍ ትችላለህ፡፡ የራስህን እንደነዚህ አይነት ምሳሌዎች ማምጣት እንደምትችል ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ በየጊዜው ስህተቶች ያጋጥሙሀል ለችግሩ ዋናኛ ተጠያቂ ራስህ ሆነህ ሳለ ራስህን ተጠያቂ ላለማድረግ ራስን መሸወጃ ሰበቦችን ትፈጥራለህ።

ድክመትንና ሽንፈትን መቀበል
የአስተማማኝ እና የዘላቂ ደስታ ቅድመ ሁኔታ ነው።ከዚህ እውነታውን ከመቀበል ጎን ለጎን ጥቁር ሳጥንም ያስፈልግሀል። ልክ እንደ አቬዬሽኑ አንተም የራስህን ጥቁር ሳጥን ገንባ። ትላልቅ ውሳኔዎችን በምትወስን ጊዜ ሁሉ በአዕምሮህ ውስጥ የሚንሸራሽረውን ሀሳብ -ፃፍ፡፡ ቅድመ - ግምቶችን፣ አማራጭ ሀሳቦችን፣ መደምደሚያዎችን ወዘተ፡፡ በኋላ ውሳኔህ መጥፎ ውጤት ካመጣ ወደኋላ ተመለስና የበረራ መረጃህን (የግልህን ጥቁር ሳጥን) መርምር፡፡ ለስህተት የዳረገህ ነገር ምን እንደሆነም ከመዘገብከው ነገር ውስጥ ፈልፍለህ አውጣ፡፡

በዚህ ደረጃ ቀላል ነው፡፡ በሰራሃት እያንዳንዷ ስህተት ልክ ሕይወትህ እየተሻሻለ ይሄዳል፡፡ ስህተትህን ማወቅ ካልቻልክ ግን ወይ አለምን ወይም ደግሞ እራስህን መረዳት አልቻልክም ማለት ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ የት ጋር አረጋገጥህ እንደተሳሳትክ የማታውቅ ከሆነ፣ እንደገና በአፍጢምህ መደፋትህ አይቀርም፡፡ ጉዞህን በመተንተን ውስጥ መፅናት ከዚህ ሁሉ ያወጣሃል፡፡ ይህ የጥቁር ሳጥን አሰራር ለግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ለድርጅትም ይሰራል። ለየትኛውም ድርጅት የሚስማማ መለመድ ያለበት አሰራር ነው፡፡

እውነታን መቀበልና የጥቁር ሳጥን አስተሳሰብ በራሳቸው በቂ አይደሉም። ስህተቶችህን ማረም አለብህ። ራስህን እያሻሻልክ መሄድ ይጠበቅብሃል፡፡ ቻርሊ ሙንገር እንዳለው “መፈታት የሚችልን ችግር እርምጃ ሳትወስድበት ምንም መደረግ የማይችልበት ሁኔታ ላይ እስኪደርስ የምትጠብቅ ከሆነ፣ አንተ የደረሰብህ ችግር የሚገባህ ሞኝ ሰው ነህ ማለት ነው፡” ውጤቱ እስኪመጣ አትጠብቅ፡፡ “እውነታን ተቀብለህ ማድረግ ያለብህን ካላደረግክ እውነታ እንደፈለገች ታደርግሃለች”፡፡ (አሌክስ ሃሌ)

✍️ ሮልፍ ዶብሊ
The art of clearly thinking

አንድ ሰው ከአንተ ጋር እያወራ፣ስልክህ ላይ ማፍጠጥ ነውር ነው።Sagal Jama
29/10/2023

አንድ ሰው ከአንተ ጋር እያወራ፣ስልክህ ላይ ማፍጠጥ ነውር ነው።
Sagal Jama

አንዳንዶች ይህ ውሸት ነጭ ነውበማለት ሊያታልሏችሁ ይሞክራሉ።
26/10/2023

አንዳንዶች ይህ ውሸት ነጭ ነው
በማለት ሊያታልሏችሁ ይሞክራሉ።

የተሳካላቸው ሰዎች መንቀሳቀስ ቀጥለዋል። ይሳሳታሉ፣ ግን አያቆሙም!!!
23/10/2023

የተሳካላቸው ሰዎች መንቀሳቀስ ቀጥለዋል።
ይሳሳታሉ፣ ግን አያቆሙም!!!

Sagal Jama follow and like my page🙏🙏🙏
19/10/2023

Sagal Jama
follow and like my page🙏🙏🙏

በ 3 ነገሮች እንዳታፍሩ1.ደሃ ጓደኞች ምክንያቱም በጓደኝነት ውስጥ ምንም አይነት ደረጃ ስለሌለ2.ያረጁ ልብሶች ምክንያቱም ልብሶች ማንነትን ስለማይገልፁ 3.በእድሜ ገፋ ያሉ ወላጆች ምክንያቱ...
16/10/2023

በ 3 ነገሮች እንዳታፍሩ
1.ደሃ ጓደኞች ምክንያቱም በጓደኝነት ውስጥ ምንም አይነት ደረጃ ስለሌለ
2.ያረጁ ልብሶች ምክንያቱም ልብሶች ማንነትን ስለማይገልፁ
3.በእድሜ ገፋ ያሉ ወላጆች ምክንያቱም አሁን የቆማችሁት በነሱ ነውና!!!

Sagal Jama Follow and share
13/10/2023

Sagal Jama
Follow and share

Address

Bole
Addis Ababa
01

Telephone

+14408053539

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sagal Jama posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sagal Jama:

Share