የስኬት መአዛ Aroma of success

የስኬት መአዛ Aroma of success የስኬት ቴክኒኮችና አጋጣሚዎች፣ የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮ ፣ አነቃቂ ጥቅሶች አና አባባሎች ተካተውበታል ።

ክፍል ፪______2.ለሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት፦እባካችሁ የራሳችሁን ምቾት ብቻ አትመልከቱ በክርስቶስ ፊት ሁላችንም ለፍርድ እንቆማለንና። ዛሬ አይናችሁ ማየት ካልቻለ ነገን አትጠቀሙበት...
27/09/2025

ክፍል ፪
___
___
2.ለሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት፦
እባካችሁ የራሳችሁን ምቾት ብቻ አትመልከቱ በክርስቶስ ፊት ሁላችንም ለፍርድ እንቆማለንና። ዛሬ አይናችሁ ማየት ካልቻለ ነገን አትጠቀሙበትም። ዛሬ ነው ለእውነት ማድላት ያለባችሁ ነገ የኛ አይደለምና።
___
የሚገርመው ነገር አባቶቻችን እንዲህ እየታዘዙም ስድቡ እንኳን በቀረላቸው። እንደሌሉም ይቆጠራሉ እኮ። ጊዜ የሰጠው ቅል እንደተባለው ነው። የጊዜ ባለቤት እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነውና ሲፈርድ አንድ ስብስብ ብቻ የሚጠየቅ እንዳይመስላችሁ በግል እንጂ። ይሁንና ግን ከአሁን ፊት እነሱ የሉም እየተባሉ ሲሰደቡ ዝም ያልኩት የሰው ክብሩ ቢዋረድ ለክርስቶስ በሚል አልፌው ነበር። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲደምሰስ ግን ዝም አልልም።
___
የሚጠብቀን ቸር ጠባቂያችን "ኖላዊ እግዚአብሔር" እያለልንና ሌላ ጠባቂ ሳንሻ፣ ስለምን በነፃነት ወንጌልን እንኳን እንዳንሰማ ተከለከልን? በገዛ በዓላችን ተፈትሸን መግባታችን ሳያንሰን ወንጌል መከልከላችን ተገቢ አይደለም።
___
መስማት ካልፈለጋችሁ ለምን መጣችሁ? ወይም ከደበራችሁ ሂዱ አልልም። ምክንያቱም የመጣችሁት ወንጌል ለመስማት አይደለማ! ወንጌል ሲነገር ለማስቆም እንጂ። ከዚያም ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን አትሰብክም ብላችሁ ለመክሰስ፣ ሲያልፍም ምእመኖቿን የበአል ሰውና እውቀት የሌለው ለማድረግ።
___
3. ሌሎች ዝም ብላችሁ የተሰየማችሁ መጀመሪያ ለክርስቶስ መታዘዝ እንዳለባችሁ እወቁ።
እወቁ፦
"የቤተ ክርስቲያን ራሷ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህችን ቤተ ክርስቲያን በራሱ ጊዚ ይጠግናታል። እናንተ ግን እወቁ በተለይ ኦርቶዶክሳዊ ሆናችሁ በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማራችሁ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሸቀጣችሁን ዘርግታችሁ የምትነግዱ አቁሙ። በፈራጁ ፊት ስትቆሙ በተገለጠው ያልታመናችሁ፣ በሚመጣው እንዳታፍሩ፣ እጣ ፈንታችሁ የሀሰት አባት በሚታየው ብልጭልጭ አለም የሚሸውደው የጨለማው ነዋሪ የዲያብሎስ ተገዢዎች በሆናችሁ ጊዜ ምን ታመካኙ ይሆን? አልሰማንም እንዳትሉ መምህራንና መጻሕፍት ነበሩ ከለከላችኋቸው እንጂ። በሚያልፍ ቀን ውስጥ የማያልፈውን ጽድቁን ሸምቱ እንጂ ከክፋ አትተባበሩ።
" ምስጋና ለበአሉ ባለቤት ሁሉን ለፈጠረው እግዚአብሔር ይሁን አሜን።"
[email protected]

ክፍል ፩___"አምና ዝም ብለናል፣ ዘንድሮም ደገምነው፣ ቀጣይስ?""በማናለብኝነት እየተከበረ ያለው የመሰቀል በአል አሁናዊ ሁኔታ"___በተለይ የሚዲያ ባለሙያዎች እና እጃችሁ ያለበት አካላት በ...
27/09/2025

ክፍል ፩
___
"አምና ዝም ብለናል፣ ዘንድሮም ደገምነው፣ ቀጣይስ?"
"በማናለብኝነት እየተከበረ ያለው የመሰቀል በአል አሁናዊ ሁኔታ"
___
በተለይ የሚዲያ ባለሙያዎች እና እጃችሁ ያለበት አካላት በሚገባ አንብቡልኝ ይህ መልእክት ለናንተ ነውና።
___
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትመራው በመንፈስ ቅዱስ እንጂ በግለሰቦች እና እኛ እንዳልናችሁ ሁኑ በሚሉት አካላት አይደለም።
___
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን መንግስታት የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር እኔ ላደራጅ፣ አንዳንድ ወጪዎችን ልሸፍንላችሁ ነገር ግን መርኀ ግብራችሁን እኔ ባልኩት ምክር ብቻ አስኪዱ የሚል ድብቅ የነበረው አጀንዳ በይፋ እየተተገበረ ሲሄድ፣ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተሰገሰጉት የገንዘብ፣ የፍርሃት፣ የሀሰትና የስልጣን ተገዢዎች በዝምታ እሰይ እያሉ እናንተንም አስተዳደርናችሁ እያሉ "እንኳን አደረሳችሁ" በሚል የፌዝ ቃል ሊደልሉን መንታ ምላሳቸውን ይመዝዛሉ። ይታወቅልኝ ሁሉንም እያልኩ አይደለም። እነዚህ ግለሰቦችና ስብስቦች ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለመንግስት ተገዢዎች ናቸው። ለመንግሥት አጀንዳ አስፈፃሚነት ቤተ ክርስቲያን ትከፍላቸዋለች። ከእናቷ ሆድ ወጥታ ሳይሆን "ከእናቷ ሆድ ገብታ እናቷን ትማታ" በሚል ቢሆን ምሳሌው ይገልፃቸው ነበረ።
___
ወደ ዛሬው አጀንዳዬ ስገባ ለተከታታይ አመታት አባቶች እና ልዑካን መዘምራን እና ምዕመናን በተመቻቸው ሰዓት ⌚ መርኀ ግብራቸውን ከማስኬድ ይልቅ በሰዓት ጉዳይ እንዲጨነቁ እየተደረገ ይገኛል።
___
በጭንቀትና በፀሐይ በደመራ ቦታ ሲደርሱና መርኀ ግብራቸውን ሲጀምሩ ደግሞ አንዳንዶች መጥተው ለፎቶና ለፖለቲካ ትርፍ ስግጥ ይላሉ። ፎቶአቸውን እንደጨረሱ መርኀ ግብሩ እንዲፈጸም ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ።
ታዲያ በዛሬው የደመራ በአል አከባበር ላይ የታዘብኩትና ያዘንኩትን በሚከተሉት ነጥቦች ላይ በስፋት እና በጥንቃቄ ታይቶ ለወደፊቱ ፎእንዲስተካከል በአክብሮት እጠይቃለሁ።
1. ለሚዲያ ባለሙያዎች፦
=> ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የበአሉ በዩኔስኮ መመዝገብ አለመመዝገብ ትርፍ ነገሯ ነው። የበአሉ ባለቤትን ለአለም መግለጥ ግን ዋነኛ አላማዋ ነው። ከዚህ ተነስታችሁ የበአሉን ታሪክ በትክክል ሳይሸራረፍ ሙሉን በእለቱ ከሚሰጥ ትምህርት ወይም እንደዛሬው ወንጌል እንዲቋረጥ ከተደረገ ከሊቃውንት በመጠየቅ በጽሑፍም ሆነ በቪዲዮ ማጋራት አለባችሁ።
=> ይህ በአል የጋራ ታሪክ አይደለም። የክርስቶስ አካል የሆነችው የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እውነት። የኢየሱስ ክርስቶስ ተአምር እንጂ። በተለመደ ቃል የመስቀሉ በአል "የሰላም፣ የአንድነት፣ የይቅርታ" በሚል ብቻ እና "በደማቅ ሁኔታ፣ በሚያምር ድባብ" በሚል የበአሉ ደጋፊ እንጂ ዋና ክፍል ባልሆኑት ቃልና ተግባራት ብቻ የሚገለጥ አይደለም። የበአሉ ዋና ክፍልም ደመራ ለኩሶ መበተን አልነበረም። በደመራው ምክንያት "ወንጌልን መስበክ፣ ጸሎት መጸለይ እና ምስጋና ማቅረብ" ነበሩ እንንጂ።
* ምስጋናው በፀሐይ ቢሆንም የበአሉ ባለቤት ደመና አምጥቶ አመስጋኞችን ቢሸፍንና በሰላም ቢያልቅም፣
* ወንጌል ግን በ9ንኛው ደቂቃ እንዲቋረጥ ታዟል፣ አባታችን መምህራችንንም አሳፍረዋል።
* እግዚኦታውም ቢሆን በጸሎት ተመስጦ ሳይሆን "መጡብህ" በሚመስል ሁኔታ አንደኛውን እግዚእ ኦ ሳልጨርስ ሦስተኛው እግዚእ ኦ፣ አንደኛው በእንተ ማርያም ላይ ሳልደርስ ፍፃሜው ላይ ነበረ። እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ትውፊት ተከብሯል እያልከኝ ነው?🤔
___
ክፍል ፪ ይቀጥላል...

31/01/2023

መልካም ጥያቄ ነው።መልሱ እንደሚከተለው ቀርቧል:_

አስቸኳይ የመንግሥት ምላሽ የሚፈልጉ የኦርቶዶክሳዊያን ፯ቱ ጥያቄዎች
1. በሕገመንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚያጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ::

2. ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ::

3. ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት እንዲታደጉ::

4. በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኀበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ::

5. እስከ አሁን የተፈጸሙ ጥቃቶች በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሱ::

6. በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ::

7. “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ::

16/06/2021
Eery morning when you weak up, say the following words for your self.
02/06/2021

Eery morning when you weak up, say the following words for your self.

(ለጠቅላላ እውቀት)◦○◎◉◎○◦
08/11/2020

(ለጠቅላላ እውቀት)◦○◎◉◎○◦

ውድ ጓደኛዬ ዘመን ሲቀያየር የማትቀየር/ሪ፣ ኃላፊ ለሆነችው ለዚህች ዕለት ብየ አንተን/ቺን አልረሳም።  ሁሌም በውስጤ እያሰብኩህ/ሽ እኖራለሁ። ባገኘሁህ/ሽ ዕለትም በጣም ደስ ይለኛል።ዘመናት...
11/09/2020

ውድ ጓደኛዬ ዘመን ሲቀያየር የማትቀየር/ሪ፣ ኃላፊ ለሆነችው ለዚህች ዕለት ብየ አንተን/ቺን አልረሳም። ሁሌም በውስጤ እያሰብኩህ/ሽ እኖራለሁ። ባገኘሁህ/ሽ ዕለትም በጣም ደስ ይለኛል።

ዘመናትን መቀያየር ፣ የኛንም ሕይወት መወሰን ፣ መስጠትና መንሳት ፣ ጥሩ ጓደኛ መስጠት ሌላም ሌላም... ሁሉም የእግዚአብሔር ስራዎች ናቸው። የእኛ ድርሻ እርስ በእርሳችን መዋደድ ፣ መተሳሰብ ነው። ውድ ጓደኛዬ ሆይ እወድሃለሁ/ሻለሁ።

መጪው ዘመንህንም እግዚአብሔር የደስታ ፣ የስኬት ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የንስሐ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ያድርግልህ/ሽ።

🌼🌸 መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ/ሽ🌼🌸

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻 እንቁጣጣሽ 🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

I hope that the new year will be the best year of your life. May all your dreams come true and all your hopes be fulfilled!

🌻🌹🍀🌹🍀🌻🍀🍃🌿🌹🌿🌻

አዲሱ ዓመት በሕይወትዎ ምርጥ ዓመት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ሁሉም ሕልሞችዎ እውን ይሁኑ እና ሁሉም ተስፋዎችዎ ይፈጸሙ!

Your friend B@ye 👉

What Does SMART Mean?SMART is an acronym that you can use to guide your goalsetting.Its criteria are commonly attributed...
18/06/2020

What Does SMART Mean?
SMART is an acronym that you can use to guide your goal
setting.
Its criteria are commonly attributed to Peter Drucker's
Management by Objectives concept. The first known use of
the term occurs in the November 1981 issue of Management
Review by George T. Doran. Since then, Professor Robert S.
Rubin (Saint Louis University) wrote about SMART in an article
for The Society for Industrial and Organizational Psychology. He
stated that SMART has come to mean different things to
different people, as shown below.
To make sure your goals are clear and reachable, each one
should be:
Specific (simple, sensible, significant).
M easurable (meaningful, motivating).
A chievable (agreed, attainable).
R elevant (reasonable, realistic and resourced, results-based).
T ime bound (time-based, time limited, time/cost limited,
timely, time-sensitive).
Professor Rubin also notes that the definition of the SMART
acronym may need updating to reflect the importance of
efficacy and feedback. However, some authors have expanded it
to include extra focus areas; SMARTER, for example, includes
E valuated and R eviewed.
How to Use SMART
Paul J. Meyer, businessman, author and founder of Success
Motivation International , describes the characteristics of SMART
goals in his 2003 book, " Attitude Is Everything: If You Want to
Succeed Above and Beyond." We'll expand on his definitions to
explore how to create, develop and achieve your goals:
1. Specific
Your goal should be clear and specific, otherwise you won't be
able to focus your efforts or feel truly motivated to achieve it.
When drafting your goal, try to answer the five "W" questions:
What do I want to accomplish?
Why is this goal important?
Who is involved?
Where is it located?
Which resources or limits are involved?
Example
Imagine that you are currently a marketing executive, and you'd
like to become head of marketing. A specific goal could be, "I
want to gain the skills and experience necessary to become
head of marketing within my organization, so that I can build
my career and lead a successful team."
2. Measurable
It's important to have measurable goals, so that you can track
your progress and stay motivated. Assessing progress helps
you to stay focused, meet your deadlines, and feel the
excitement of getting closer to achieving your goal.
A measurable goal should address questions such as:
How much?
How many?
How will I know when it is accomplished?
Example
You might measure your goal of acquiring the skills to become
head of marketing by determining that you will have completed
the necessary training courses and gained the relevant
experience within five years' time.
3. Achievable
Your goal also needs to be realistic and attainable to be
successful. In other words, it should stretch your abilities but
still remain possible. When you set an achievable goal, you may
be able to identify previously overlooked opportunities or
resources that can bring you closer to it.
An achievable goal will usually answer questions such as:
How can I accomplish this goal?
How realistic is the goal, based on other constraints, such as
financial factors?
Example
You might need to ask yourself whether developing the skills
required to become head of marketing is realistic, based on your
existing experience and qualifications. For example, do you have
the time to complete the required training effectively? Are the
necessary resources available to you? Can you afford to do it?
Tip:
Beware setting goals that someone else has power
over. For example, "Get that promotion!" depends on
who else applies, and on the recruiter's decision. But
"Get the experience and training that I need to be
considered for that promotion" is entirely down to you.
4. Relevant
This step is about ensuring that your goal matters to you, and
that it also aligns with other relevant goals. We all need support
and assistance in achieving our goals, but it's important to
retain control over them. So, make sure that your plans drive
everyone forward, but that you're still responsible for achieving
your own goal.
A relevant goal can answer "yes" to these questions:
Does this seem worthwhile?
Is this the right time?
Does this match our other efforts/needs?
Am I the right person to reach this goal?
Is it applicable in the current socio-economic environment?
Example
You might want to gain the skills to become head of marketing
within your organization, but is it the right time to undertake the
required training, or work toward additional qualifications? Are
you sure that you're the right person for the head of marketing
role? Have you considered your spouse's goals? For example, if
you want to start a family, would completing training in your
free time make this more difficult?
5. Time-bound
Every goal needs a target date, so that you have a deadline to
focus on and something to work toward. This part of the
SMART goal criteria helps to prevent everyday tasks from taking
priority over your longer-term goals.
A time-bound goal will usually answer these questions:
When?
What can I do six months from now?
What can I do six weeks from now?
What can I do today?
Example
Gaining the skills to become head of marketing may require
additional training or experience , as we mentioned earlier. How
long will it take you to acquire these skills? Do you need further
training, so that you're eligible for certain exams or
qualifications? It's important to give yourself a realistic time
frame for accomplishing the smaller goals that are necessary to
achieving your final objective.

Source......

Use MindTools.com resources to learn more than 2,900 management, leadership and personal effectiveness skills, helping you to be happy and successful at work.

ውድ የፌስቡክ ፔጅ ቤተሰቦቼ ከፌስቡክ በተጨማሪ የቴሌግራም ቻነል ስለከፈትን⤵⤵⤵⤵ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ቀላልና ፈጣን መረጃን ያግኙ። ሰለተቀላቀላችሁን እናመሰግናለን። ለናንተ ይጠቅሳሉ...
18/02/2020

ውድ የፌስቡክ ፔጅ ቤተሰቦቼ ከፌስቡክ በተጨማሪ የቴሌግራም ቻነል ስለከፈትን⤵⤵⤵⤵ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ቀላልና ፈጣን መረጃን ያግኙ። ሰለተቀላቀላችሁን እናመሰግናለን። ለናንተ ይጠቅሳሉ የምንላቸውን መረጃዎች ለማድረስ ዝግጁ ነን። እናንተም መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቸሁ ማድረጋችሁን እንዳትረሱ። አንወዳችኋለን እናንተም ውደዱን!
https://telegram.me/aroma_of_success

Address

Ethiopia-Addis Ababa
Addis Ababa
2293546

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የስኬት መአዛ Aroma of success posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የስኬት መአዛ Aroma of success:

Share