Plumber

Plumber Worker

21/09/2022
20/09/2022
15/09/2022


ቻርሊ ቻፕሊን 88 ዓመታትን በህይወት ኖሯል ። ግን ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ የተወልን አራት ዓረፍተ ነገሮችን ብቻ ነው ።

1⃣ ምንም ነገር ዘላለማዊ አይደለም ፤ ሌላው ቀርቶ ችግሮቻችንም ጊዜያዊ ናቸው ።

2⃣ በዝናብ ውስጥ መሄድ እወዳለሁ ፣ ምክንያቱም ማንም እንባዬን አያይብኝምና ።

3⃣ በህይወታችን ታላቁ የባከነው ቀን ሳንስቅ የዋልንበት ቀን ነው ።

4⃣ በአለም ላይ ምርጥ ስድስት ዶክተሮች:-
#⃣ ፀሀይ
#⃣ እረፍት
#⃣ የሰውነት እንቅስቃሴ
#⃣ አመጋገብ
#⃣ የራስ-ክብር
#⃣ ጓደኞች

👍እነዚህን ጠብቃቸውና ህይወትህን አስደሳች አድርገው ።

👉ጨረቃን ካየህ ፥ የተፈጥሮን ውበት ታያለህ ፣
👉ፀሀይንም ካየህ፣ የፈጣሪን ኃይል ታያለህ ፣
👉 መስተዋት ካየህ ፣ የፈጣሪን ትልቅ ጥበብና ፍጡር ታያለህ ስለዚህ በፈጣሪህ እመን ።

✅✅ እኛ ሁላችንም ቱሪስቶች ነን ፣ የጉዞ ወኪላችን ፈጣሪ ነው ። እሱም የመጓጓዣ ቆይታችንን ፣ የመስተንግዶ ሁኔታችንንና መዳረሻችንን ሁሉ የሚያውቀው እመነውና በህይወት ደስተኛ ሁን!! ህይወት ጉዞናት እናም ዛሬን በአግባቡ ኑራት ነገ ላትኖር ትችላለህና!! የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን!!!
═════════❁✿❁ ═════════

11/09/2022
27/08/2022

አማራ ሆይ ቀሪ ጊዜ ያለህ እንዳይመስልህ!

በዚህች ከክር በቀጠነች ጊዜ ውስጥ እርስ በእርስህ ከተጠላለፍክ እና እራስህን ከሌሎች የተለየ አድርገህ ከቆጠርክ ጠላት በላይህ ላይ ሀውልት ሰርቶ ታሪክ ሆነህ ትቀራለህ።

አዎ ጠላት ህጻን፣ መነኩሴ፣ ነፍሰጡር ሳይል ከቀናው አንበርክኮ ሊገዛህ፤ ካልቀናው ደግሞ አጥፍቶህ ሊጠፋ ደጃፍህ ደርሷል።

ጠላት ሳይቀበር በቀላችንን ሳንወጣ ጠላት አማራ ምድርን እንደከበበ እያወቅን መሪያችንን ስንረግም እንውላለን።

አሁን እየተሰራ ያለውን ድንቅ ገድል እና ጀግንነት በቃላት መግለፅ የማይቻል ቢሆንም፤ ጦርነት ተለዋዋጭ ነውና እንደራጅ፤ አካባቢያችንን እንጠብቅ!ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያወጣው መግለጫ

አሸባሪው ሕወሓት የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አባብሶ ቀጥሏል።

አሸባሪው ሕወሓት የሰላም አማራጮችን ሁሉ ረግጦ የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አባብሶ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

አገልግሎቱ ባወጣው መግለጫ አሸባሪው ሕወሓት የተዘረጋለትን የሰላም አማራጭ ረግጦ ለሦስተኛ ጊዜ በሀገራችን ላይ የከፈተውን ወታደራዊ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሎበታል ብሏል፡፡

አሸባሪው ለሰላም የተዘረጋውን መንገድ ትቶ፣ በሙሉ አቅሙ ለጦርነት ሲዘጋጅ መቆየቱ ይታወቃልም ነው ያለው።

አሁንም በተለያዩ ግንባሮች የከፈተውን ጥቃት አድማሱን በማስፋፋት ለፍቶ አዳሪ ንጹሐን ዜጎችን ዒላማ እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል።

ጊዜ ያለፈበትን የሰው ማዕበል የጦርነት ስልት በመከተል በሺዎች የሚቆጠሩ አዳጊዎችንና ወጣቶችን በገፍ እየማገደ፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ዛሬም አጠናክሮ ቀጥሏልም ነው ያለው በመግለጫው፡፡

ሕወሓት ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የንብረት ማውደም፣ መሠረተ ልማት የማፈራረስና መሰል የጭካኔ ተግባራትን ለመፈጸም እንደ ከዚሀ ቀደሙ ሁሉ ኃይል አሰባስቦ ወደ አማራና አፋር ክልል አዋሳኞች እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አንስቷል።

መገግሥት የዘረጋው የሰላም አማራጭ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይሀ አሸባሪ ቡድን የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት በተሟላ ብቃት በመመከት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስታወቀው።

27/08/2022

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ!

አሸባሪው ሕወሐት በአንድ በኩል የተለመደውን የሰው ኃይል ማዕበልን በመጠቀም የቆቦ ከተማ ከውጭ በብዙ አቅጣጫ እያጠቃ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ በከተማ ውስጥ ሠርጎ ገቦችን በማሥረግ የሕዝቡን ደኅንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል።

የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን በመልቀቅ እና ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል።

አሸባሪው ኃይል የትግራይን ወጣት እየማገደ በሕዝብ ማዕበል ማጥቃቱን ካላቆመ መከላከያ ሕጋዊ ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ ግዴታውን ለመወጣት የሚገደድ ይኾናል።

ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓም
አዲስ አበባ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address

Bure

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Plumber posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Plumber:

Share