South design and construction supervision enterprise

South design and construction supervision enterprise South Design and Construction Supervision Enterprise (SDCSE) is a Level-1 Engineering
Consultancy Firm founded in September 2011.

ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ጋር የሥራ ስምምነት በመፈጸም የከርሰምድር ውሃ ጥናት ማከናወን ጀመረ። ****በቅርቡ እንደ አዲስ ተደራጅቶ በአጭር ቀናት ው...
16/02/2024

ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ጋር የሥራ ስምምነት በመፈጸም የከርሰምድር ውሃ ጥናት ማከናወን ጀመረ።
****
በቅርቡ እንደ አዲስ ተደራጅቶ በአጭር ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ የገባው ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ ከሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ጋር የሥራ ውለታ በመፈጸም ወደ ተግባራዊ እንቀስቃሴ ተሸጋግሯል። ኢንተርፕራይዙ በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ የከርሰ ምድር ውሃ መጠን እና መገኛ ጥልቀት ጥናት ለማከናወን የሳይት ርከክብ ያደረገ ሲሆን በክልሉ በብቸኝነት ባለቤት በሆነው ጂኦ-ፊዝክስ መሳሪያ በመታገዝ ጥናቱን በይፋ አስጀምሯል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ/ም
ሀዋሳ

ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በይፋ ተመስርቶ ስራ መጀመሩን የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አስፋው ጎኔሶ ገለጹ።****የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት መመስረት በማስመልከት ...
19/01/2024

ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በይፋ ተመስርቶ ስራ መጀመሩን የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አስፋው ጎኔሶ ገለጹ።
****
የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት መመስረት በማስመልከት በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና የሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አስፋው ጎኔሶ መግለጫ ሰጥተዋል።

የቦርድ ሰብሳቢው በመግለጫቸው ሲዳማ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ የዳበረ ልምድና ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች፣ በዘመናዊ ጥናትና ዲዛይን መስሪያ መሳሪያ እንዲሁም በብቁ ማኔጅመንት አባላት መደራጀቱን ገልጸው፤ የክልሉ መንግስት ኢንተርፕራይዙ ያዳበራቸውን ተሻጋሪ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን በማስፋትና ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችሉ ጠንካራ ውሳኔና ድጋፍ በመስጠት እንዲቋቋም ማስቻሉን ገልጸዋል።

የኢንተርፕራይዙ መቋቋሙ እንደ ክልል ለጀመርናቸው የብልፅግና ጉዞ መረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው ያሉት ሰብሳቢው፣ ድርጅቱ በክልሉና ከክልሉ ውጪ የሚገነቡ የግንባታ ሥራዎች ጥራታቸውን ጠብቀው ለትውልድ ተሻጋሪ ሆነው እንዲገነቡ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት ዘርግቶ እንደሚንቀሳቀስ ገልጸዋል። ድርጅቱ በዋነኝነት የመስኖ፣ የመጠጥ ውሃ ፣ የመንገድና የሕንጻ ግንባታ ሥራዎች ወጪ ቆጣቢ የተሻለ ጥራትና ቅልጥፍና ያላቸው ሆነው እንዲገነቡ ብቃት ያለው የጥናት፣ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራዎችን እንዲያከናውን በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት መቋቋሙን አንስተዋል።

በመጨረሻም የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አስፋው ጎኔሶ መንግስታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አልሚዎች፣ እንዲሁም ሌሎች የልማት አጋሮች ያሏቸውን አንገብጋቢ የልማት ጥያቄዎችን በፍጥነት ለመፍታት ከኢንተርፕራይዙ ጋር አብረው እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል ሲል የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዘግቧል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እየተገነቡ በሚገኙ መስኖ ተቋማት አፈጻጸም ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ።*********ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል...
17/10/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እየተገነቡ በሚገኙ መስኖ ተቋማት አፈጻጸም ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
*********
ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖ ተቋማት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር የሥራ ውለታ በመግባት እያማከራቸው ከሚገኙ 12 አነስተኛ መስኖ ተቋማት ግንባታ ቁጥጥርና ኮንትራት አስተዳደር ፕሮጀክቶች ዙሪያ የሚመክር የምክክር መድረክ በተርጫ ከተማ ተዘጋጅቷል።

በክልሉ በደቡብ ዲዛይን አማካሪነት ስር በመገንባት ላይ የሚገኙ 12 የመስኖ ፕሮጀክቶች ( ቡቢ፣ ቡኒ፣ ከነቺ፣ ኦፊያ፣ ዳማ፣ ኦልሙ፣ ፐቱ፣ መራቻ፣ ሻፓ፣ ጽልቤ፣ ቶኒ እና ውኒ) ሥራ ወቅት ያጋጠሙ ውጫዊ ችግሮች፣ በአማካሪ፣ በአሰሪና በተቋራጭ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ችግሮች ዙሪያ ማብራሪያ ቀርቧል።

አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ፣ ፕሮጀክቶቹ ተጨማሪ የዲዛይን ማሻሻያ የሚፈልጉ ሆኖ መገኘት እና የተሻሻለ ዲዛይን በወቅቱ አጠናቆ አለማቅረብ፤ ተቀብሎም በፍጥነት ምላሽ አለመስጠና ክፍያዎችን በወቅቱ አለመፈጸም እና የተቀናጀ የሥራ ግንኙነት ሥርዓት አለመጠንከር በጉድለት ተነስቶ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በበጋ ወራቶች ተጨማሪ ሀብትና በጀት ለፕሮጀክቶቹ በማፍሰስ ሥራውን ማፍጠን እንደሚገባ፣ ውሎችን ዳግም በመከለስ ለተሽከርካሪና ሌሎች ግብዓቶች ወቅቱ የሚጠይቀውን ተመጣጣኝ ክፍያ በማቅረብ የግንባታ ቁጥጥርና ኮንትራት አስተዳደር ስራውን ከዚህ በበለጠ ማሻሻል ይገባል በማለት ምክረ ሀሳብ ተሰጥቷል።

የክልሉ መስኖ ተቋማት አስተዳደር ኤጀንሲ የሥራ ኃላፊ የሆኑትና በመድረኩ የተገኙት አቶ አሸናፊ ሽብሬ ለለውጥ እንስራ ሲሉ አጸንኦት ሰጥተው ተናግራዋል።

አቶ አሸናፊ የግንባታ ግብዓት በተለይ አሸዋ በሚቀርብበት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባና የተሟላ ምርመራ ማድረግ መዘንጋት የለበትም በማለት ለዚህም ልምድና ብቃት ያለቸውን ተቆጣጣሪ መሃንዲስ መድቦ በኃላፊነት ስሜት መስራት ያስፈልጋል በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

ከመስኖ ግንባታ ቁጥጥርና ኮንትራት አስተዳደር ሥራዎች በተጨማሪ በተርጫ ከተማና በተርጫ ዙሪያ ወረዳ 4ት ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ጥናት ድራፍት ሪፖርት ቀርቦ ገለጻ ተደርጓል። ከገለጻው በኋላ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን አስተያየቶችን በማካተት የተጠናቀቀ የጥናት ዶኩመንት በአጭር ጊዜ እንዲቀርብ ከስምምነት ተደርሷል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት መስኖ ልማት ኤጀንሲ የጋራ ምክክር አደረጉ።****ደብብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅትና የሲዳማ መስኖ ልማት ኤጀ...
21/09/2023

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት መስኖ ልማት ኤጀንሲ የጋራ ምክክር አደረጉ።
****
ደብብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅትና የሲዳማ መስኖ ልማት ኤጀንሲ የጋራ ምክክር ያደረጉት በ4ት ኮንትራት የታቀፉ 19ኝ የመስኖ ግንባታ ቁጥጥር ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ነው።

ደቡብ ዲዛይን ከኤጀንሲው ጋር የሥራ ውለታ በመግባት እየሰራቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል አምስቱን ማለትም ጫላ፣ ላሌኖ፣ ዳጊያ፣ ሶዎ እና ኤሬረ ቤበኮ አነስተኛ የመስኖ ግንባታ ቁጥጥር ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃቱን በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።

ሁለት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ሌሎች የተቀሩት አዲሎ፣ አሳሮ፣ ኤሬርቴ፣ ተርጪጫ፣ ቲሺሼ እና የብላቴ ወንዝ ጎርፍ መከላከያ ግንባታ በመልካም አፈጻጸም ላይ ስገለጽ፤ የተቀሩት ስድስት ፕሮጀክቶች (ቡሉታ፣ ሻፋሞ፣ ዋሞሌ፣ ቡሊቻ፣ ደሴና ጋራና አነስተኛ መስኖ) አፈጻጸም አመርቂ አለመሆኑን በድርጅቱ ተለይቶ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ባለሙያዎች ለቀጣይ ሥራ ግብዓት የሚሆን ገንቢ አስተያየት እና ጥያቄ ማንሳት ችለዋል።

በመድረሱ ኤጀንሲውን ወክለው የተገኙት አቶ መስፍን በላይ መስሪያ ቤታቸው ደቡብ ዲዛይን ላስመዘገበው መልካም ሥራ አፈጻጸም ዕውቅና ይሰጣል ያሉ ሲሆን በሥራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት በማረም ግንባታዎች በጥራት፣ በጊዜና በተያዘላቸው የወጪ መጠን በማጠናቀቅ ለሚፈለገው የልማት ዓላማ ማዋል እንዲቻል ምክክር መድረኮች ከዚህ በተሻለ ሁኔታ መጠናከር አለባቸው በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅና የመስኖና ማጠንፈፍ ዋና ሥራ ሂደት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሔለን ዮሐንስ በበኩላቸው የሲዳማ ክልል መስኖ ኤጀንሲ በድርጅታችን ላይ አመኔታ በመጣል አብረውን ስለሚሰሩ እናመሰግናለን በማለት የተሰጡ አስተያየቶች በቀጣይ አፈጻጸሞቻችንን ለማሻሻል ስለምጠቅሙን በአዎንታ ተቀብለን ለተሻለ ለውጥ እንሰራለን ብለዋል። ምክትል ሥራ አስኪያጇ፡ አገልግሎታችንን ይበልጥ ለማሻሻል ኤጀንሲው ክፍያዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲፈጽምላቸው በመጠየቅ ለወደፊቱ አሰሪውና አማካሪው ከዚህም በተሻለ መናበብና መቀናጀት ያስፈልገዋል ሲሉ አክለዋል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የአራቱም ክልሎች የጋራ ሀብት ሆኖ ህብረተሰቡን በእኩልነት እያገለገ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በአመታዊ ትምህርታዊ ጉዛ የሃላላ ኬላ ፓርክን ጎበኘ።*****የድርጅቱ ሠራተኞችና አመራር አካላት የተጠናቀቀውን ዓመት ሥራ አፈጻጸም በመገምገምና ቀጣይ ...
07/08/2023

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በአመታዊ ትምህርታዊ ጉዛ የሃላላ ኬላ ፓርክን ጎበኘ።
*****
የድርጅቱ ሠራተኞችና አመራር አካላት የተጠናቀቀውን ዓመት ሥራ አፈጻጸም በመገምገምና ቀጣይ ዓመቱ ዕቅድ ላይ ከተወያዩ በኋላ ወደ ሃላላ ኬላ በማቅናት ፓርኩን ጎብኝተዋል።

ሠራተኛው በስራ የደከመ አዕምሮ በማንቃት በታደሰ መንፈስ ለቀጣይ ሥራ ዝግጁ ማድረግ ያለመ መደበኛ የትምህርት ጉዞ አካል በሆነው በዚህ ዓመት ትምህርታዊ ጉዞ ወደ ሃላላ ኬላ ፓርክ ጉዞ ማድረግ ተችሏል።

በጉዞው የተሳተፉ የተቋሙ ሠራተኞች በፓርኩ ጉብኝት መደሰታቸውንና በገበታ ለአገር ፕሮግራም በተገነባው በዚህ ስፍራ የተመለከቷቸው የተለያዩ የግንባታ ጥበብ የታነጹ መሠረተ ልማቶች ለቀጣይ ስራዎቻቸው ትምህርት እንደሰጣቸው ተናግረዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያስጠናው 1220 ሄ/ር የሚያለማ የአነስተኛ መስኖ ጥናትና ዲዛይን ሪፓርት ቀርቦ ተገመገመ***የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር...
26/06/2023

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ያስጠናው 1220 ሄ/ር የሚያለማ የአነስተኛ መስኖ ጥናትና ዲዛይን ሪፓርት ቀርቦ ተገመገመ
***
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ጋር በመተባበር ያስጠናው የአነስተኛ መስኖ ልየታ፣ ሰርቨይና አዋጭነት እንዲሁም ዝርዝር ኢንጂነሪንግ ዲዛይን ጥናት ሪፖርት ቀርቦ ግምገማ ተደርጓል።

ጥናቱ በ15 ወረዳዎች የተካሄደ ሲሆን 1,220 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችል ነው።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ከክልሉ መንግስት መስኖ ልማት ኤጄንሲ ጋር በአጠቃላይ 18 ፕሮጀክቶች ላይ ጥናት ለማካሄድ ውለታ ገብቶ ስራውን በማከናወን አጠናቆ ያቀረበ ሲሆን የተመረጡ ሰባት ናሙና ፕሮጀክቶች ለግምገማ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ለግምገማ የቀረቡ ፕሮጀክቶች ገበታ (አርቤጎና ወረዳ)፣ ቡናቃ(ጭሬ)፣ ጊኦ(ወንሾ)፣ ጌዲዮ(ወንሾ)፣ ሻዳዳ(ሻፋሞ)፣ ማልጋንቾ(ሁላ)፣ እና ሎሎኮ(ዳራ) ናቸው።

በመድረኩ የተሳተፉት የአሰሪው አካል አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ተጠቃሚ የህብተሰብ ክፍሎች የጥናት ሪፖርቱን ከተቹ በኋላ፤ አስተያየት የተሰጠባቸው ሃሳቦች ተካተው የተሻሻለ የጥናት ሰነድ በአስቸኳይ ለኤጀንሲው እንዲቀርብ አሳስበዋል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ነባሩን ደቡብ እንዲሁም አዳዲሶቹን ክልሎች በጋራ እያገለገ ይገኛል።

የደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራ አመራር ቦርድ የተለያየ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ።***የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ ተሰብስቦ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ...
28/03/2023

የደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ሥራ አመራር ቦርድ የተለያየ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳለፈ።
***
የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ ተሰብስቦ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል።

ቦርዱ የ2015 በጀት ዓመት የተከለሰ ዕቅድና የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ውባየሁ ትዕዛዙ በኩል ቀርቦ አድምጧል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ በተከለሰ ዕቅድ 409 ፕሮጀክቶችን በመስራት 243,387,560 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደሥራ መግባቱን በሪፖርቱ አመላክቷል።

ድርጅቱ በስድስት ወራት 223 ፕሮጀክቶችን በመከወን 80,918,091 ብር በመሰብሰብ 65.6% መፈጸም መቻሉን ሥራ አስኪያጁ አክለዋል።

በመቀጠልም የ2014 በጀት ዓመት የውጪ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ አድምጧል።

ቦርዱ ከቀረቡለት ሪፖርቶች እያደገ የመጣ አፈጻጸም መመልከቱን ገልጾ ለዚህም የተቋሙ አመራር እና ሠራተኛ ዕውቅና ልሰጠው ይገባል ሲል አድናቆቱን ገልጿል።

የሥራ አመራር ቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ዓለማየሁ ባውዲ፣ የድርጅቱን የማስፈጸም አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን እንዲሁም ያሉትን ዕድሎች ሁሉ አሟጦ መጠቀም እንደሚገባ አንስተዋል።

አክለውም ድርጅቱ አዳዲስ ክልሎች እኩል ትኩረት በመስጠት፤ በአስተዳደራዊ ወሰን ሳይታጠር ህብረተሰቡን ማዕከል አድርጎ ያለልዩነት እንዲያገለግል አሳስበዋል።

በቀረበው የውጪ የኦዲት ሪፖርት መነሻም በህብረት ስምምነቱ ላይ በተቀመጠው አሰራር መሠረት ለድርጅቱ ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዝና አንድ ከግማሽ ቦነስ እንዲከፈል ይሁንታ ሰቷል።

ሌሎች የተዘጋጁ የሰው ሃይል፣ የግዥ፣ የንብረት እና የበጀት አስተዳደር መመሪያዎችን በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ድጋሚ በመሰብሰብ ውሳኔ ለማሳለፍ ቀነ ቀጠሮ በመያዝ ተለያይቷል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል የተጠናው የ15 አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን ድራፍት ሪፖርት ለግምገማ ቀረበ።*****ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ለግምገማ ያቀረበው ከ...
23/02/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል የተጠናው የ15 አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን ድራፍት ሪፖርት ለግምገማ ቀረበ።
*****
ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ለግምገማ ያቀረበው ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር የስራ ውለታ በመግባት ጥናት ሲያካህድ የቆያቸውን 15 አነስተኛ መስኖ ጥናትና ዲዛይን ስራ ነው።

ጥናቱ ለግምገማ የቀረበው የአሰሪው ኤጀንሲ ሥራ ኃላፊዎች ፣ የዞን አመራሮችና የሚመለከታቸው ሠራተኞች እንዲሁም ከፌደራል መንግስት የተጋበዙ የዘርፉ ባለሙያዎችና ተጋባዥ ሙሁራን በተገኙበ ነው።

ኤጀንሲው: ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር አዲሱን ክልል በመልካም ሁኔታ እየደገፈ መሆኑን በመጥቀስ ሰፊ ጥናት አካሂዶ ለማስገምገም በመብቃቱ ምስጋናውን አቅርቧል።

ጥናቱ መዘግየቱን በማንሳትም በቀረበው ሪፓርት የተሰጡ የግምገማ አስተያየቶችን በማካተት በአጠረ ጊዜ የመጨረሻ ሰነድ እንድቀርብለት ጠይቋል።

የ15ቱ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶች ጥናት የተካሄደው በክልሉ ስድስት ዞኖች ነው። እነዚህም በበንቺ ሸኮ ዞን ባርካ፣ እሸቴ፣ ቤርጊ፤ በሸካ ዞን ገንጂ፤ በምዕራብ ኦሞ ዞን መልካ፤ ዳውሮ ዞን ዛይር፣ ዳሊ፣ ማሳሊ፣ ፋንታ፤ ኮንታ ዞን ዲቦ፤ ከፋ ዞን ጪሊ፣ ኩጳ፣ ጎንዶሮ፣ ዱዲይ እና ኪቻኒ ፕሮጀክቶች ናቸው።

በደቡብ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ክልል በ15 ከተሞች የተካሄደው የመጠጥ ውሃ ጥናት ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ።*******ድርጅታችን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር ውለታ በመግባ...
21/02/2023

በደቡብ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ክልል በ15 ከተሞች የተካሄደው የመጠጥ ውሃ ጥናት ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ።
*******
ድርጅታችን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር ውለታ በመግባት በክልሉ ስድስት ዞኖች ስር በሚገኙ 15 ከተሞች ያካሄዳቸው የውሃ ምንጭ ልየታ፣ የአዋጭነትና ዝርዝር ኢንጂነሪንግ ዲዛይን ጥናት አጠናቆ ለአሰሪዎች በማቅረብ አስገምግሟል ።

በይርጋዓለም ከተማ በተደረገው በዚህ መድረክ ጥናቱ በክልሉ ስር ባሉ ስድስት ዞኖች በሚገኙ ቴፒ፣ ቆንዳ፣ ዳካ፣ ቢጣ፣ ዣዥ፣ መስከረም ፍሬ፣ ሎማ ባሌ፣ አንጌላ፣ ሰንጌቲ፣ ደልብ ገነት፣ አንቻኖ ገነት፣ ድሽ፣ ብሬ፣ ማጂ እና ጋችት ከተሞች መከናወኑን ተገልጿል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በከተሞቹ ያጠናውን ዝርዝር ጥናት ሪፓርት የአሰሪው ክልል ዞኖች የውሃና ኢነርጂ መምሪያ ሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ያቀረበ ስሆን ተሳታፊዎች በጥናት ድክመንቱ ያዩትን ጭብጦች በማንሳት የግምገማ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት በአጭር ጊዜ የመጨረሻ የተጠቃለለ የጥናት ሪፓርት እንድቀርብለት በማሳሰብ ግምገማው ፍጻሜውን አግኝቷል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር የስራ ውለታ ተፈራረመ።******ድርጅቱ ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር የተፈራረመው የስራ ውል በጨለለቅቱ ከተማ የንፁህ መ...
11/01/2023

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር የስራ ውለታ ተፈራረመ።
******
ድርጅቱ ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር የተፈራረመው የስራ ውል በጨለለቅቱ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ቁጥጥርና ኮንትራት አስተዳደር የማማከር ስራ ለማከናውን መሆኑን ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ዜጎችን የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ፤ በጥናትና ዲዛይን፣ ግንባታና በግብዓት አቅርቦት በርካታ ስራዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በኩል እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

የ4 ከተሞች የውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን ረቂቅ ሪፖርት እየተገመገመ ይገኛል።*******በደቡብ ክልል ውሃ ቢሮ አሰሪነት በቁሊቶ፣ ወናጎ፣ በቶ እና ጠበላ ከተሞች በደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ...
02/01/2023

የ4 ከተሞች የውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን ረቂቅ ሪፖርት እየተገመገመ ይገኛል።
*******
በደቡብ ክልል ውሃ ቢሮ አሰሪነት በቁሊቶ፣ ወናጎ፣ በቶ እና ጠበላ ከተሞች በደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የተሰራ የውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን ተጠናቆ ለአሰሪው ሪፖርት ቀርቦ እየተገመገመ ይገኛል።

የሪፖርት ግምገማ መድረኩ በሻሸመኔ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን በተጠናው ጥናት ግኝት ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው የሚገኘው።

"ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃል የዓለም ፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ**** በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ፣ በሀገራችን ለ18ኛ እንዲሁም በክልላችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለምአቀ...
29/11/2022

"ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃል የዓለም ፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ
****
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ፣ በሀገራችን ለ18ኛ እንዲሁም በክልላችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው ዓለምአቀፍ የፀረሙስና ቀን በድርጅታችን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል።

"ሙስና መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው በዘንድሮው በዓል: የድርጅቱ አስተዳደር አካላትና ሠራተኞች ከሙስናና ብልሹ አሰራሮች ራሳቸውን ለማራቅ፣ ሌሎችም ሲፈጽሙ በተግባር ለመታገልና ለማጋለጥ ግንዛቤ ወስደዋል።

በዕለቱ በድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን፣ የጥያቄና መልስ ውድድር፣ መጣጥፎች እንዲሁም ለተሳታፊዎች የስጦታ ሽልማት መርሃግብር ተከናውኗል።

ደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት
ህዳር 20/2015 ዓ/ም

Address

Hawassa University Avenue
Hawassa
116

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South design and construction supervision enterprise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to South design and construction supervision enterprise:

Share