Hayle. Fetmaso Buliko

Hayle. Fetmaso Buliko Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hayle. Fetmaso Buliko, Home improvement, Jinka.

02/03/2020
02/03/2020
20/02/2020
20/02/2020

ሮዝመሪ (የጥብስ ቅጠል)

ሮዝመሪ በደማቅ አረንጓዴ ቀለሙ፣መርፌ በሚመስል ቅጠሉ እና ለየት ባለው ማዕዛው ይታወቃል፡፡ ሮዝመሪ በመላው ዓለም ለምግብ በሚሰጠው ጥፍጥና በእጅጉ የታወቀ ቢሆንም ያዛኑ ያህል ለሕክምና አገልግሎት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ የቅመም አይነት ነው፡፡ ሮዝመሪ ቅጠሉ ደርቆና ተወቅጦ በየትኛውም የምግብ አይነት ውስጥ መጨመር ሲቻል እርጥቡንም እንደዚሁ በተለያዩ ምግቦች ውስጥ ጨምሮ መመገብ ይቻላል፡፡ አልፎ አልፎ የተጨመቀ ዘይቱን ማግኘት ከተቻለ ደግሞ ሌላው ወሳኝ አማራጭ ነው፡፡ በመሆኑም ሮዝመሪ በሳይንስ የተረጋገጡ ቀጥሎ ያሉትን የጤና ጠቀሜታዎችን ይሰጣል፡፡

1. የአንጎል ተግባርን ያሻሽላል፡- ጥንታዊያን ግሪኮችና ሮማውያን ሮዝመሪ የማሰብ ብቃትን እንደሚያጎለበት ደርሰውበት የነበሩ የመጀመሪያ ሕዝቦች ናቸው፡፡ የሮዝመሪ ቅጠል ወይም ዘይት ማሽተት ለነገሮች ያለንን ጥኩረት ይጨምራል እንዲሁም መረጃዎችን የማስታወስ ብቃት እንደሚያሳድግ የዘመኑ ሳይንስ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል፡፡ በዕድሜ መግፋት ለሚከሰት መጃጀትና የመርሳት ዕክል መፍትሄ ሰጭ እንደሆነ ተመስክሮለታል፡፡

2. የፀጉር ዕድገትን ያፋጥናል፡- ሮዝመሪ ዘይት በውስጡ በያዘው ኬሚካላዊ ንጥረ ነገር የፀጉር መርገፍና መነቀል እንዲሁም ያለ ጊዜው የሚከሰት ራሰ በረሃነትን ይዋጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የራስ ማሳከክና ይከላከላል፡፡

3. ስቃይ ወይም ሕመምን ይቀንሳል፡- በባህላዊ ሕክምና ውስጥ ሮዝመሪ መለስተኛ ሕመምን በማስታገስ ረገድ የታወቀ ነው፡፡ አኩፓንቸር ለተሰኘ ባህላዊ የደረቅ መርፌ ሕክምናም ሆነ ለሌሎች ተመሳሳይ ሕመሞች ሮዝመሪ ዘይት በተወጋው መርፌ ላይ ማፍሰስ ወይም መቃባት ስቃይን ይቀንሳል፡፡ ሳይንስ እንዳረጋገጠው የሮዝመሪ ዘይት ሕመምን በተሰማን ቦታ ላይ መቀባት ዘማናዊ ከሆነው አሲታሚንኦፊን ከተሰኘ መድኃኒት የተሻለ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡

4. ደም መጣጭ ነፍሳትን ይመክታል፡- ሮዝመሪ ዘይት ቤት ውስጥ ብንረጭ ደም መጣጭ የሆኑ አደገኛ ባክቴሪያና ቫይረስ የሚያሰራጩ የወባ ትንኝ፣ትኋን፣ቅማል፣መዥገር የመሳሰሉ ሌሎች ነፍሳትን ያባርራል፡፡ በነገራችን ላይ ዘመናዊ የተባይና ነፍሳት መርጫ ኬሚካሎች በተወሰነ መልኩ የሮዝመሪ ዘይት የተካተተባቸው ነው፡፡

5. ጭንቀት ያባርራል፡- ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ተማሪዎች ከፈተና በፊት የሮዝመሪ ዘይት ወይም ቅጠል ደጋግመው ቢያሸቱ ኮርትሶል የተሰኘ አደገኛ የሰውነታችንን ሆርሞን በመቀነስ ውጥረትና ጭንቀታቸውን ትርጉም ባለው ደረጃ ይቀንስላቸዋል፡፡

6. የደም ዝውውር ይጨምራል፡- የእግርና የእጅ ጣቶቻቸው የሚቀዘቅዝባቸው ሰዎች በሮዝመሪ ዘይት ወይም ቅጠል ቢያሹት ከችግራቸው እንደሚላቀቁ ሳይንስ አረጋግጧል፡፡

7. የአጥንት መገጣጠሚያ መቆጣትን ይቀንሳል፡- ሮዝመሪ ዘይት የአጥንት መገጣጠሚያዎች በመቀባት የአጥንት ብግነትና የአጥንት መገጣጠሚያ ሕመም ይቀንሳል፡፡

8. ካንሰር፣የምግብ መመረዝ፣የጉበትና የስርዓተ ልመትን ጤና በመጠበቅ ረገድ ሮዝመሪ ከፍተኛ አስተዋፆ አለው፡፡

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው

© Hakim-bet.com

13/02/2020

Address

Jinka
00NO

Telephone

+251916546170

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hayle. Fetmaso Buliko posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share