Herbicide Company

Herbicide Company የሰብሎችን ጤና መጠበቅ የአለማችንን የብክለት መጠን መቀነስ ነውና እንጠቀም

05/07/2025

ሸርና ላይክ በማድረግ አበረታቱን?

አሜን አሜን አሜን ክቡርነትዎ
12/25/2022

አሜን አሜን አሜን ክቡርነትዎ

የህይወትም ውጣ ውረድ  ጫወታ እንደአለም ዋንጫ በ90 ደቂቃ በተጠናቀቀ!!!
12/18/2022

የህይወትም ውጣ ውረድ ጫወታ እንደአለም ዋንጫ በ90 ደቂቃ በተጠናቀቀ!!!

12/04/2022

"አውራ የሌለው ንብ ሲበተን አውራ ያለው ዝንብ ወረረው"
ጀግናው ጀኔራል

ግብርና መር የኢትዮጵያው የኢንዱስትሪ አብዮት ይፋፋም።
08/03/2022

ግብርና መር የኢትዮጵያው የኢንዱስትሪ አብዮት ይፋፋም።

ከሞታችን አብሮ እርሻውም እንዳይሞት!!!!
06/22/2022

ከሞታችን አብሮ እርሻውም እንዳይሞት!!!!

ወንድማችን በጣም ደስ ይላል። በርታ አንድ የቢሊዮኖች መጀመሪያ ነው።
03/19/2022

ወንድማችን በጣም ደስ ይላል። በርታ አንድ የቢሊዮኖች መጀመሪያ ነው።

የምታጭደው የዘራህውን ነው! ስትንከባከብ ታነፃለህ!!መልካም ቀን ተመኘንላችሁ!
10/15/2021

የምታጭደው የዘራህውን ነው! ስትንከባከብ ታነፃለህ!!መልካም ቀን ተመኘንላችሁ!

"ክተት!!"“በአማራ ክልል ውስጥ ማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሳሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ [ከዛሬ] ጀምሮ ይክተት” ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማ...
07/26/2021

"ክተት!!"

“በአማራ ክልል ውስጥ ማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሳሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ [ከዛሬ] ጀምሮ ይክተት” ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። አሸባሪው ትህነግ በተለያዩ ግንባሮች ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ የማጥቃት ሙከራ እያደረገ ነው ብለዋል። ሕዝቡ ከጎናችን እንዲሆን ባስተላለፍነው መልዕክት በአሁኑ ወቅት በሁሉም ረገድ ከጎናችን ሆኗል ነው ያሉት። ለመላው የክልሉና የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋና ይገባዋልም ብለዋል።

የክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች ለክልሉ መንግሥትና ለጸጥታው ኃይል ያደረጉት ድጋፍ የክልሉን መንግሥት አኩርቷል ነው ያሉት። የአማራ ክልል ባለሀብቶችና የንግዱ ማኅበረሰብ እያደረጉት ላለው ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ከተሠለፈብን ጠላት አኳያ ብዙ ኃይል የምናሰልፍበትና ሎጅስቲክስ የሚያስፈልግ ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ የክልሉ ሕዝብና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ያሰዩት ምላሽ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል። ክልሎች እያደረጉት ያለው ድጋፍ ታሪካዊ ነውም ብለዋል።

የክልሉ ተመላሽ የሠራዊት አባላትና የጦር መኮንንኖች ሠራዊቱን ተቀላቅለው እየተፋለሙት እንደሚገኙም ገልጸዋል። አሸባሪው ትህነግ በውጊያው ከሕፃናት እስከ አዛውንት ድረስ እያሰለፈ ነው፣ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን እያስጨረሰ ነው፣ ጦርነት የማያውቁ ሕፃናት ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ጉዳት እየደረሰባቸው ነውም ብለዋል፡፡

የትህነግ ዓላማ የአማራን ሕዝብ ለማጥቃትና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ያለመ ስለመሆኑም ተናግረዋል። ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ነው ብለዋል። በራያና በጠለምት ግንባሮች የጁንታው ጀሌዎች እንደ ቅጠል እየረገፍ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት እየታገለ የመጣ ጀግና ሕዝብ ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ አማራ ማን እንደሆነ ያውቁታል፣ ይህን ሕዝብ ለማንበርከክ የትኩረት አቅጣጫ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነውም ብለዋል።

አሸባሪውን ቡድን የአፋርና የአማራ ሕዝብ እየተፋለመው ነውም ብለዋል። በሕዝቡ፣ በልዩ ኃይሉና በመከላከያ ሠራዊት ትህነግን የመምታት ሥራ እየተሠራ እንደሆነም ተናግረዋል። ይህ ኃይል እስካልጠፋ አናርፍም ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ። የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣ ጦርነቱ የአማራን ሕዝብ ሕልውና የምንታደግበት ነውም ብለዋል።

የሕልውና ጦርነቱን በአሸናፊነት ለመጨረስ የአማራ ሕዝብ አስተዋጽኦ የጎላ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ርእሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው በክልሉ ውስጥ የማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሣሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከዛሬ ሐምሌ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ማዕከል እንዲከት የክተት ጥሪ ተላልፏል።

ሁሉም የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ለፀረ ትህነግ ዘመቻ መዘጋጀት አለበት ብለዋል። የክተት ጥሪው አማራንና ኢትዮጵያን የመታደግ ጥሪ ነውም ብለዋል። ሀገር የማፈረስ ዓላማ ያለውን ኃይል በተባበረ ክንድ መደምሰስ አለብን ነው ያሉት። አሁን በገጠምንበት አውደ ውጊያ ከፍተኛ ከሲሳራ እየገጠመው ነው፣ ወደ ትግራይ ተመልሶ መሄድ አይፈልግም፣ ምክንያቱም ለትግራይ እናቶች የሚሰጠው መልስ የለውም፣ ስለዚህ ህልሙን ማጨናገፍ አለብን ብለዋል፣ ፀረ ኢትዮጵያ የሆነውን ከሀዲ ቡድን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሁሉም መነሳት አለበት ነው ያሉት።

በአሉባልታ ሊያፈርሱን ስለሚፈልጉ ከአሉባልታ መጠበቅ ይገባል፣ በአንድነት ማሸነፍ አለብንም ብለዋል። በሁሉም ግንባር የጠላትን ኃይል ዋጋውን እየሰጠነው ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ሕዝቡ ከጎናችን መሆኑን መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

ኅብረተሰቡ መረጃ እንደሚያስፈልገው እናውቃለን ነገር ግን ሁሉም የጦርነት መረጃ ስለማይነገር በትዕግሥት መጠበቅ ይገባል፣ አስፈላጊ መረጃ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ይሰጣልም ብለዋል። መረጃ ከትክክለኛው አካል መውሰድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሁሉም ሕዝብ በትህነግ ፕሮፖጋንዳ ሳይደናገጥ የቡድኑን እኩይ ድርጊት መታገል እንዳለበትም ገልጸዋል። ሠርጎ ገብነት ላይ ሕዝቡ እንዲጠነቀቅም አሳስበዋል፣ የትግራይ ሕዝብ ወንድማችን ነው፣ ትግሬ የሆነ ሁሉ ጠላታችን አይደለም፣ በትህነግ ፕሮፖጋንዳ ተሳስቶ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ እየተዋጋ ነው፣ አሁንም መላው የትግራይን ሕዝብ አይወክልም ነው የምንለው፣ ነገር ግን የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ወደጦርነት ከማሰለፍ መታቀብ አለባቸው፣ የትግራይ ሕዝብ ታሪካዊ ስህተት እየፈፀመ ነው፣ ወያኔን በቃህ ማለት አለበት፣ በክልላችን የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በሰላም እንዲኖሩ እንፈቅዳለን፣ ለጠላት የሚያብሩ ካሉ ግን ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን ነው ያሉት።

የአማራን መሬት ለወያኔ እሾህ እናደርገዋለን፣ በየትኛውም አቅጣጫ ሊንቀሳቀስ እይችልም፣ ሁሉም በየደረጃው መደራጄት አለበት፣ ወደ ግንባርም መሄድ አለበት ነው ያሉት። ተመላሽ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የጀመሩትን አኩሪ ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። ወቅቱ ለአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ወቅት ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ ታሪክ የምንሰራበት ነው፣ ባንዳን መቅበር ደግሞ የአማራ ሕዝብ እንደሚያውቅበት ገልጸዋል።

(አሚኮ)

ጥራት መለያችን ፔጃችንን ይቀላቀሉ
07/02/2021

ጥራት መለያችን ፔጃችንን ይቀላቀሉ

የተባረከ ሰንበት ይሁንላችሁ
06/27/2021

የተባረከ ሰንበት ይሁንላችሁ

Address

Adis Abeba, Bahir Dar, Debre Markose Enjibara
Shreveport, LA
71107

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Herbicide Company posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Herbicide Company:

Share

Category